Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Oslo St. Lideta LeMariam Church est à l'adresse suivante:
Consultez la carte pour voir où vous pouvez trouver un Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Oslo St. Lideta LeMariam Church.
Les catégories suivantes décrivent Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Oslo St. Lideta LeMariam Church:
Consultez le site Web suivant pour Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Oslo St. Lideta LeMariam Church:
Voici comment les autres visiteurs ont noté le Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Oslo St. Lideta LeMariam Church:
Que s'est-il passé à Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Oslo St. Lideta LeMariam Church récemment? Ici vous pouvez voir les nouvelles pertinentes:
የቤተክርስቲያን አባልነት Read more at www.lidetalemariam.no 1.የቤተክርስቲያን አባልነት አስፈላጊነት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “መልካም እረኛ እኔ ነኝ አብም እንደሚአውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃቸዋለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል..........ድምፄንም ይሰማሉ” ዮሐ 10፤14-15 እንዳለው ካህን ወይም ቄስ መንጎቹን ካላወቀና እነርሱም እረኛቸውን /አባታቸውን/ እስካላወቁ ድረስ የእረኝነት ሥራ የለም። ለዚህም ነው ጌታችን ቅዱስ ጴጥሮስን ሦስት ጊዜ ያህል “በጎቼን ፤ ጠቦቶቼን እና ግልገሎቼን አሰማራ”ያለው ። ዮሀ 21 እውነተኛ እረኛ በጎቹን በመልክም በድምፅም የሚያውቃቸውና እነርሱም የሚያውቁት ምንደኛ ያልሆነ በዋናው በር የሚገባው ነው። ዮሐ 10፤ እግዚአብሔር የራሱን መንጋ ያውቃል። በቤተክርስቲያን ጥላ ውስጥ የሚኖሩ የቤተክርስቲያን አባላት ሁሉ የእግዚአብሔር መንጋዎች ናቸው።እኒህ አባላት ቤተክርስቲያን ይባላሉ።የምዕመናን ስብስብ (ኤክሊሲያ)ይባላል።በቤተክርስቲያን አባልነት ውስጥ በቃለ አዋዲ ሥርዓት ያልተመዘገቡ ግን የክርስቲያን አባላትና የእግዚአብሔር ተከታዮች ለማለት በቂ ማረጋገጫ አልተሰጠም። ስለሆነም የሃይማኖት አባል፤ ሃይማኖተኛ፤ ኦርቶዶክሳዊና ክርስቲያን ለመባል በግድ የቤተክርስቲአን አባል መሆን ያስፈልጋል። መዝ 90፤ 1-16 2.ቤተክርስቲያን አባል የሚያተኩርበት የቤተክርስቲያን አባል ሲባል ከቤተክርስቲያን አገልግሎት፤ ከቤተክርስቲያን አገልጋዮችና ከራሱ ምን ጥቅም እንደሚፈልግ ያገናዘበ መሆን ሲችል ነው። አንድ ሰው ከቤተክርስቲያን ምን ጥቅም ሊያገኝ ይችላል? ለምሳሌ ያህል በደስታው ጊዜ፤ በጥልቅ ሀዘኑ ጊዜ፤በችግሩ ጊዜ፤በሰርግ ፤በሞት፤በክርስትናና በተለያዩ የግልና የማህበራዊ ጉዳዮች አንድ ክርስቲያን ከቤተክርስቲያን የሚገባውን አገልግሎት ማግነት ይችላል። ይህ ሲባል ግን ቤተክርስቲያንም ከምዕመኑ የሚፈልገውን የአባልነት መንፈሳዊ ግዳጅ ያሟላ መሆን አለበት እንጂ እንዲሁ የእግዚአብሔር ቤት ስለሆነች ብቻ የነፃ አገልግሎት ለዘፈቀደው ነዋሪ ሁሉ የማዳረስ ግዳጅ አልተጣለባትም። ምንም እንኳን አለአድልዎ ለሁሉም ወንጌልን እንድትሰብክና ፈውስ እንድታዳርስ ተልዕኮና አደራ የተጣለባት ቤተክርስቲያን ብትኖረንም አንድ አንዶች ከላይ የተጠቀሱ ስጋዊ ሁነታዎች ገጠሞች ከሌላቸው በቀር ሁሌም ከራሳቸው ሚጠበቀውን የማያሟሉ በመሆናቸው እንዲህ ያሉትን የቤተክርስቲያን አገልግሎት ሳይገባቸው አገልግሎቷን በእኩሌታ የማዳረስ ግዳጅ አልተጣለባትም። ለዚህ ሲባል ነው ቀኖና ቤተክርስቲያን የተሰራው። በቀኖና ቤተክርስቲያን ድንጋጌ ክርስቲያንና በቤተክርስቲያን ተጠቃሚ የሚሆኑ ሁሉ መስፈርት አላቸው። "የአባልነት መታወቂያና የአባልነት ክፍያ የማያሟሉ ሁሉ ቤተክርስቲያን አታውቃቸውም" የሚለውን ጨምሮ ሌሎች አብይ ነጥቦችን ትኩረት መድረግ ግድ ይላል። ሌላው ከቤተክርስቲያን አባቶች የሚገኘውን ጥቅም ማወቅ ነው። አንድ ክርስቲያን የሃይማኖቱ አባል እስከሆነ ድረስ ቤቱ መጎብኘት ጠበል መረጨት/መጠመቅ/ አለበት። ለመንፈሳዊነት እስከተዘጋጀ ድረስም ከአበ ነፍሱ ንስሀ መቀበልና ለቅዱስ ቁርባን እራሱን ማብቃት ይችላል። ይህ ባልተሟላበት ሁኔታ ከመዳን ዋና አላማ ውጭ ሆኖ የህዝብ ቁጥር ከፍ ማለት ብቻ ከቤተክርስቲያን የእረንኝነት መስመር ጋር ስለማይጣጣም ሙሉ አባል አያሰኝም። 3.በቤተክርስቲያንና በሕዝበ ክርስቲያን መካከል ያለው ግንኙነት በቤተክርስቲያን ውስጥ ወጣቶች፤ ሴቶች፤ ወንዶች፤ ሰራተኞችና በተለያየ እድሜ እንዲሁም የስራና የአ እንዲሁም የስራና የአቋም ሁኔታ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ልንገናኛቸው እንችላለን። የሁሉም ስምና አድራሻ በቤተክርስቲያን ውስጥ ተመዝግቦ ሊያዝ ይችላል፡፡ ለሁሉም የሚሰጠው አገልግሎት መንፈሳዊና ተመሳሳይ ብቻ ስለሆነ ሁሉም የሚጠብቀው ከቤተክርስቲያን ሥርአት አኳያ የሚገኘውን መንፈሳዊ ጥቅም ብቻ ሊሆን ይገባል። 4. የቤተክርስቲያን አባላት ልዩ መለያ በጥምቀት ተወልዶ ሀብተወለወድና ስመ ክርስትና የተቀበለ ሁሉ የቤተክርስቲያን አባል እንደሆነ ይታመናል። “ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል” ተብሏልና ማር 16፤16 በእድሜና በፆታ፤በስራና በትምህርት በሌሎችም ሁኔታዎች ያለን ልዩነት የቤተክርስቲያንን አባልነትና የክርስቶስ አካል የመሆን ምልክቶች አይደሉም። የቤተክርስቲያን ልዩ መለያዎች የሚባለው መንፈሳዊነት ብቻ ነው። የተጠመቁ አባላት፤ ንስሃ የገቡ የሚቆርቡና በተእግስታቸውና በምግባር አርአያነታቸው የሚገለጹ፤ በትጋህ በጾም በፀሎትና በማህበራዊ ተሳትፎ ንቃታቸው የሚለኩ ትሁታን እኒህ የሃይማኖት አባላት ናቸው። የስም ክርስቲያን በመሆን ቅዳሴ የማያስቀድሱትን፤ ትምህርተ ወንጌል የማይማሩትን፤ የቤተክርስቲያንን መርሃግብር የማይከታተሉትን ሁሉ ግን የቤተክርስቲያን አባል ለማለት እውነት ይቻላልን? መንፈሳዊ የቤተክርስቲያን ኣባላት አንኳን አዋቂዎች ሕጻናቱም አርአያቸው ይሰብካል። በአለባበሳቸው፤ በአነጋገራቸው፤በተስፋቸው፤ በአመጋገባቸው በሌሎችም የዕለት ተዕለት ኑሯቸው ሁሉ እግዚአብሔርን ይገልጹታል። እንዲህ በተግባር የሚገለጽ ማንነት የያዘ ነው የቤተክርስቲያን አባል ተብሎ የሚታወቀው። ይቀየጥላል።.......................
Worthy to listen and to be save and blessed! https://www.youtube.com/watch?v=vc_2luNGHBI
St Gabriel annual celebration in Oslo!!
Til alle, ha en fin dag forysatt! Amen!
የተከበራችሁ የማሕደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ምእመናን በሙሉ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተከታታይ ባደረግነው የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ መሠረት የፊታችን እሁድ ከቅዳሴ በኋላ ያለፈውን ዓመት የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርትና የሒሳብ ሪፖርት ስለምናቀርብ የቤተክርስቲያኗ አባላት የሆናችሁ በሙሉ በቤተክርስቲያን በመገኘት ሪፖርቱን እንድታደምጡና በሪፖርቱ ዙሪያ ያላችሁን ጥያቄና አስተያየት እንድትሰጡ በአክብሮት ተጠርታችኋል። ለሪፖርቱ ሲባል ቅዳሴ ከወትሮው ቀደም ብለን የምንገባ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ መግለጽ እወዳለን። የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር።
Adrese : Caspar Storms vei 12, 0664 Oslo Fra bussterminal/Helsfyr buss100 og av Fjellhus FRA Helsfyr buss 66 og av på Caspa Storms vei
የማጥመቅና የፈውስ አገልግሎት በቀሲስ መንግስቱ ጥላሁን (የእናቴ ልጅ)። ከስኞ 6. mai 2019 ዓ/ም ጀምሮ ለሦሥት ሳምንታት በሥራ ቀናት በተከታታይ ዘወትር ጠዋት ከ07:00 እስከ 12:00 ሰዓት ድረስ በቤተ ክርስቲያናችን ቀሲስ መንግስቱ ጥላሁን የማጥመቅና የፈውስ አገልግሎታቸውን ያከናውናሉ። ስለሆነ ምዕመናንና ምዕመናት በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት በመገኘት የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የደብሩ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ በማክበር ይጋብዛል፡፡ ከሌላ አካባቢ ለመምጣት የምትፈልጉ ምዕመናንና ምዕመናት በይበልጥ መረጃ ለማግኘት ያግኙን (Kontakt oss) ገጻችንን ይመልከቱ። http://www.lidetalemariam.no/
ኦስሎ ማህደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ዓመታዊ በዓል 2011ዓም!!
ሆሳንእና በአርያም(3)
መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡- መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው” /መዝ. 86፥1/ ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም፤ በእመቤታችን ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ፡፡ በግንቦት 1 ቀን /5ሺ ከ5መቶ የመከራው ዘመን ሊያልቅ 15 ዓመታት ሲቀሩት/ ሊባኖስ በሚባል ተራራ ከፀሐይ የምታበራ ሴት ልጅ ተወለደች፡፡ ይህቺውም ፍጥረት ሁሉ /ደቂቀ አዳም ሁላቸው/ ተስፋ ሲያደርጓትና ሲጠባበቋት የነበረች የድኅነታቸው ምልክት እመቤታችን ናት፡፡ የዘንድሮው የእመቤታችን የድንግል ማርያም የልደት ክብረ በዓል በደብራችን በማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የሃገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁእ ኣቡነ ኤሊያስ፣ ኣባቶች ካህናትና መምህራነ ወንጌል በተገኙበት ግንቦት ፫ እና ፬ (May 11 &12-2019) በታላቅ ድምቀት ይከበራል። በመሆኑም በደብራችሁ በኦስሎና ኣከባቢው የምትገኙ ምዕመናን በዚህ በዓል ላይ ተገኝታችሁ የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። "እናታችን ቅደስት ድንግል ማርያም ሆይ የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው " አድራሻ፦Caspar Storms vei 12, 0664 Oslo ለበለጠ መረጃ በዚህ ይደውሉ (+47) 946221386፣ 94213469፣91773031፣ 93990534፣95421568፣45572710 ኢሜይል፡ [email protected] ድረ ገጻችን፣ www.lidetalemariam.no
ዜና ቤ/ክ የጸሎትና የሃዘን መግለጫ ሥነ ሥርዓት የወጣት አማኑኤል ተክሌን ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ምክንያት በማድረግና እንዲሁም በአገራችን በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET 302 ላይ በደረሰው አደጋ ላይ ህይወታቸውን ላጡ መንገደኞች በነገው ዕለት ዕሑድ 17. mars ከቅዳሴ በኋላ ከ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የጸሎትና የሃዘን መግለጫ ሥነ ሥርዓት የሚካሄድ መሆኑን እየገለጽን በኦስሎና አካባቢው የምትገኙ ምዕመናንና ምዕመናት በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት በመገኘት በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንድትካፈሉ የደብሩ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ በማክበር ይጋብዛል። አድራሻ Caspar Storms vei 12, 0664 Oslo, 4. etg. Minnestund Ifm. Dødsfallet av unge Amanuel Tekle og de 157 passasjerer og mannskapet som har mistet livet i flystyrten av Ethiopian airlines flight nr. ET 302, skal det avholdes bønn og minnestund i morgen 17. mars kl. 11:00 etter Gudstjeneste. Adresse: Caspar Storms vei 12, 0664 Oslo, 4. etg. Menighetsrådet.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የእስካንዲኒቢያን ሀገረ ስብከት የመጀመሪያውን ስብሰባ አካሄደ። በአውሮፓ አኅጉር በአዲስ መልክ ከተዋቀሩት አራት ሀገረ ስብከቶች አንዱ የሆነው የእስካንዲኒቢያን ሀገረ ስብከት ሀገረ ስብከቱን በአዲስ መዋቅር ለመዘርጋትና ለማጠናከር መጋቢት 6 እና 7 ቀን 2011 ዓ/ም (15. og 16. mars 2019) ለሁለት ቀን የቆየ ስብሰባ በሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ሰብሳቢነት በስዊድን እስቶክሆልም መንበረ ጵጵስና በደብረ ሰላም መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተካሂዷል። ጉባዔው በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሥራ አስፈጻሚ አባላትንም መርጦአል። 1ኛ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ 2ኛ መልአከ ብርሃን አባ ገብረጊዮርጊስ ካሣዬ 3ኛ መልአከ ጽዮን አባ ሙሴ ኃይለሚካኤል 4ኛ ወ/ሮ ረቂቅ ጉልላት 5ኛ አቶ አበበ ተፈሪ 6ኛ አቶ ሰለሞን ተዘራ
Ici vous pouvez trouver des photos de Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Oslo St. Lideta LeMariam Church:
Ici vous pouvez trouver des vidéos de Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Oslo St. Lideta LeMariam Church:
Epiphany celebration in Bergen.
ጥምቀት በበርገን ፣ኖርዌይ ፣ጥር ፪ሺ፲፩
የዘንድሮ 2011 ዓ/ም የታህሳስ ወር የታላቁ መልአክ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አከባበር! የዘንድሮ 2011 ዓ/ም የታህሳስ ወር የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በቤተ ክርሥቲያናችን (Caspar Storms vei 12, 0664 Oslo) በዕለተ ቀኑ ዓርብ ታህሳስ 19 ቀን ከጠዋቱ 07 ሰዓት ጀምሮ በማህሌት፣ በንግሥ፣ በዝማሬና በቅዳሴ የሚከበር በመሆኑ በኦስሎና አካባቢዋ የምትገኙ ምዕመናንና መዕመናት በተጠቀሰው ቀን፣ ቦታና ሰዓት ተገኝታችሁ የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የደብሩ የሰባካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ በማክበር ይጋብዛል። በዓሉ በዕምነታቸው የጸኑ የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች የነበሩ ሦሥቱ ወጣቶችን (ሰለስቱ ደቂቃን) አናንያን (ሲድራቅ) ፤ አዛርያንና (ሚሣቅ) ፤ ሚሣኤልን (አብድናጎ) ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ከዕሳት ነበልባል የታደጋቸውን ቀን ምክንያት በማድረግ የሚዘከርበት ዕለት ነው። ት/ዳንኤል 3፡1-30
የጸሎትና የቅዳሴ ቅበላ ተከታታይ ትምህርት ሰሞኑ ልናጠናው የሚገባ ቀጥሎ ያለው ነው። ኩሉ ዘገብራ ለጽድቅ ጻድቅ ውእቱ ወዘያከብር ሰንበተ ኢይበል ፈላሲ ዘገብአ ኀበ እግዚአብሔር ይፈልጡኒኑ እምህዝቡ ፣ኩሉ ዘገብራ ለጽድቅ ጻድቅ ውእቱ ወዘያከብር ሰንበተ
Vérifiez également ce Restaurants à proximité:
Vérifiez également ce Hôtels à proximité:
Vérifiez également ce Agents immobilier à proximité:
Vérifiez également ce Salons de coiffure à proximité: